ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/ይህ ሁሉ ክ ፉ ነ ገ ር እ ን ዲኖር የ ሚፈቅ ደ ውን እ ግ ዚአ ብሔር እ ን ዴት ልወደ ው እ ችላ ለ ሁ?

ከGospel Translations Amharic

ዘልለው ለመሐድ፦የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

Related resources
More By John Piper
Author Index
More About The Gospel
Topic Index
About this resource
English: For Your Joy/How Can I Love a God Who Allows so Much Evil?

© Desiring God

Share this
Our Mission
This resource is published by Gospel Translations, an online ministry that exists to make gospel-centered books and articles available for free in every nation and language.

Learn more (English).
How You Can Help
If you speak English well, you can volunteer with us as a translator.

Learn more (English).

By John Piper About The Gospel
Chapter 5 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው

Translation by Desiring God


እናንተ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፣ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው፡፡
ዘፍጥረት 5ዐ፡2ዐ
በእርግጥ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ አንተ በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ለማሤር ተሰበሰቡ፤ ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈፀም ነው፡፡
ሐዋርያት ሥራ 4፡27-28፡፡
‹‹ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው››
ዘዳግም 29፡29፡፡

ስለክፉ እንዲሁም ስለስቃይ ልናገር የምችለው ተመራጭና ትልቅ ነገር፣ እግዚአብሔር በኢየሱስ በከል ገብቶ ወደመልካምነት የለወጠው መሆኑን ነው፡፡ የክፉ መነሻ ምስጢርነቱ እንዳለ ነው፡፡ ምስጢር የሆነው ነገር መጠሪያ ‹‹ነፃ ምርጫ ›› የሚል ይሆናል፡፡ ፍፁም የሆነው አንድ ፍጡር ኃጢአት መፈፀምን የመረጠበትን ምክንያት አይገልጥም፡፡ የምስጢሩ ሌላ ስም ‹‹የእግዚአብሔር ልዕልና›› የሚለው ነው፡፡ እውነትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመሆኑን ያህል፣ ይህ ምስጢርም ጥያቄዎችን ያለመልስ ይተዋቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለመሄድ የምንፈልገውን እርቀት አያስኬሄደንም፡፡ ይልቁንም እንዲህ ነው የሚለን፣ ‹‹ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው››(ዘዳግም 29፡29)

የመጽሐፍ ቅዱስ ልብና የክርስትና ልብ፣ ክፉ ከየት እንደመጣ አይገልጥም፡፡ እግዚአብሔር እንዴት በዚያ ገብቶ ፍፁም ተቃራኒ ወደሆነ ዘላለማዊ ጽድቅና ደስታ እንደሚለውጠው ነው የሚያመለክተው፡፡ ለመሲሁ እንዲህ እንደሚሆን የሚጠቁሙ ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነበሩ፡፡ የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ወደግብፅ በባርነት ተሸጠ፡፡ በአሥራ ሰባት ዓመት የተተወ መሰለ፡፡ እግዚአብሔር በሁነቱ ውስጥ ስለነበረ ግን፣ የሸጡትን ሰዎች፤ በታላቅ ርሀብ ጊዜ እንዲያድናቸው ግብፅ ውስጥ መሪ አደረገው፡፡ ታሪኩ ዮሴፍ ለወንድሞቹ እንዲህ በማለት በተናገረው ቃል ውስጥ ተጠቃሏል፡- ‹‹እናንተ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የበዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው››(ዘፍጥረት 5ዐ፡2ዐ)

ስለኢየሱስ የተነገረ ትንቢት፤ ያድን ዘንድ የተተወ ወይም የኢየሱስን ቅድመ አያቶች አስቡ፡፡ በአንድ ወቅት እግዚብሔር ብቸኛው የእሥራኤል ንጉሥ ነበር፡፡ ሕዝቡ ግን አመፁና ሰብዓዊ ንጉሥ ጠየቁ፣ ‹‹አይሆንም፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን››(1ሳሙ. 8፡19) አሉ፡፡ በኋላ ግን እንዲህ በማለት ንስሀ ገቡ፣‹‹ሌላው በደላችን ሳያንስ፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት አደረግን››(1ሳሙ. 12፡19)፡፡ እግዚአብሔር ግን በዚያውስጥ ነበር፡፡ ከነዚህ ነገሥታት ክርስቶስን ወደዓለም አመጣ፡፡ ኃጢአት የለሹ አዳኝ ኃጢአተኞችን ለማዳን ሲመጣ፣ መነሻው ከኃጢአት ውሰጥ ነበር፡፡

አስደናቂው ነገር ግን፣ ክፉው ነገርና ስቃዩ፣ እራሱን ክፉንና ስቃይን ድል ለማድረጊያነት ለክርስቶስ የተሰጠው መንገድ መሆኑ ነው፡፡ በኢየሱስ ላይ የሚፈፀም ማንኛውም የክህደት እና የጭካኔ ድርጊት ኃጢአትና ክፉ ሥራነበር፡፡ ቢሆንም እግዚአብሔር በውስጡ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ ‹‹እግዚአብሔር በጥንት ውሳኔውና በቀደመው ዕውቀቱ ይህን ሰው አሳልፎ በእጃችሁ ሰጣችሁ፤ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት›› (ሐዋርያት ሥራ 2፡23)፡፡ ጀርባው ላይ ያረፈው ግርፋት፣ የራሱ ላይ የሾህ አክሊል፣ ጉንጩ ላይ የተተፋበት ምራቅ፣ የፊቱ ላይ ሰንበር፣ እጁ የተቸነከረባቸው ሚስማሮች፣ ጎኑ የተወጋበት ጦር፣ የገዢዎች ስድብ፣ የወዳጁ ክህደት፣ የደቀመዛሙርቱ ትተውት መሄድ፡፡ እነዚህ ሁሉ የኃጢአት ውጤቶች ሲሆኑ፣ የኃጢአትን ኃይል ለማጥፊያነት በእግዚአብሔር የታቀዱ ነበሩ፡፡ ‹‹በእርግጥም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ አንተ በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ለማሤር ተሰበሰቡ፡፡ ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈፀም ነው›› (ሐዋርያት ሥራ 4፡27- 28)

የእግዚአብሔርን ልጅ ከመጥላትና ከመግደል የከፋና የገዘፈ ኃጢአት የለም፡፡ ከክርስቶስ ስቃይ የላቀ ወይም ከእርሱ የበለጠ በደል አልባነት (ንፅህና) አልነበረም፡፡ ቢሆንም እግዚአብሔር በዚያ ሁሉ ውሰጥ ነበር፣ ‹‹መድቀቁና መሰቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ዓላማ፣ ክፉና ስቃይን ማጥፋት ነበር፣›› (ኢሳይያስ 53፡1ዐ) ይህ አሠራር ታዲያ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ፣ በእረሱ በኩል ዘላለማዊ ጽድቅና ደስታ እንዳያመጣ የሚያግደው ኃጢአት ወይም ክፉ ነገር እንደሌለ እግዚአብሔር ለዓለም ያሳየበት አይደለም? በእኛ በኩል የተፈጠረው ያው ስቃይ፣ የድነታችን ተስፋ ሆነ፣ ‹‹አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ›› (ሉቃስ 23፡34)

እግዚአበሔር ሕይወትና ደስታን እንዲሰጠን አንድያ ልጁን ኢየሱስን ላከው፡፡

ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደዓለም መጣ...
1ጢሞቴዎስ 1፡15

ክርስቶስ እንደእኛ ላሉ ኃጢአተኞች መሞቱ ነው የምሥራቹ ፡፡ የሞቱን የማዳን ኃይል ዋጋ ያለው ለማድረግና የዘላለምን ሕይወት፣ እንዲሁም የደስታን በር ለመክፈት በአካል ከሞት ተነሣ፡፡ (1ቆሮንቶስ 15፡2ዐ) የዚህ ትርጉሙ፣ እግዚብሔር በደለኛ ኃጢአተኞችን ነፃ በማድረግም ፃድቅ ይሆናል ማለት ነው (ሮሜ 3፡25-26) ‹‹እንዲህም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለኃጢአት ሞቶአልና፤ ወደእግዚብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ፣ ስለአመፀኞች ሞተ›› (1ጴጥሮስ 3፡18) ወደ እግዚአብሔር መግባት ጥልቅና ዘላለማዊ እርካታ ባለበት ሥፍራ መሆን ነው፡፡

በክርስቶስ ደም ዓማካይነት የተገኙ ጥቅሞች፣ ንስሐ የሚገቡና በእርሱ የሚታመኑ ሰዎች የሚያገኙዋቸው ናቸው፡፡

በጌታ በኢየሱስ እመን፣ አንተም ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ ፡፡
ሐዋርያት ሥራ 16፡31

‹‹ንስሐ መግባት›› ማለት ፣ ውሸት ከሆኑት የኃጢአት ተስፋዎች ሁሉ መላቀቀ ማለት ነው፡፡ ‹‹እምነት›› ማለት፣ በኢየሱስ በኩል እንዲሆንልን እግዚአብሔር በሰጠን ተስፋዎች ሁሉ መርካት ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ ‹‹ ወደእኔ የሚመጣ ...ፈፅሞ አይጠማም ›› (ዮሐንስ 6፡35) ድነታችንን እራሳችን አናገኘውም፡፡ በችሎታችን ልናመጣው አንችልም (ሮሜ 4፡4-5) በእምነት ዓማካይነት በጸጋ ስጦታ ነው (ሮሜ 3፡24) ከነገሮች ሁሉ በላይ ዋጋ ከሰጠነው እናገኘዋለን (ማቴዎስ 13፡44) ይህን ስናደርግ እግዚአብሔር በፍጥረት ላይ ያለው ዓላማ ይፈፀማል—እርሱ በእኛ ይከብራል እኛ በርሱ እንረካለን—ለዘላለም፡፡