ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/ይህ ሁሉ ምን ይጠቅ መኛ ል?

ከGospel Translations Amharic

ዘልለው ለመሐድ፦የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

Related resources
More By John Piper
Author Index
More About The Gospel
Topic Index
About this resource
English: For Your Joy/What Does All This Mean for Me?

© Desiring God

Share this
Our Mission
This resource is published by Gospel Translations, an online ministry that exists to make gospel-centered books and articles available for free in every nation and language.

Learn more (English).
How You Can Help
If you speak English well, you can volunteer with us as a translator.

Learn more (English).

By John Piper About The Gospel
Chapter 7 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው

Translation by Desiring God

በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታመኑ እናንተ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፡፡
1ዮሐንስ 5፡13
ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡
ዮሐንስ 5፡24
እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፡፡
ሐዋርያት ሥራ 3፡19
ወደዘላለም ሕይወት የሚያደርሳችሁን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠብቁ ሳለ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ፡፡
ይሁዳ 1፡21

ማውጫ

እግዚአብሔር ለክብሩ ነው የፈጠረን

ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ ... ለክብሬም የፈጠርሁትን ... አምጡ፡፡
ኢሳይያስ 43፡6-7

እግዚአብሔር የፈጠረን፣ ታላቅነቱን እንድናገን ነው፡፡ መልካምነቱን፣ እውነትና ውበቱን፣ ጥበቡንና ፅድቁን እንድናሳይ ጭምር፡፡ የእግዚብሔርን ክብር የማሳያ ታላቅ ነገር የሚመጣው፣ በእርሱነቱ ሙላት ከሚሰማን ጥልቅ ደስታ ነው፡፡ የዚህ ትርጉሙ፣ እግዚአብሔር ይከብራል፣ እኛ ደግሞ ደስ ይለናል ማለት ነው፡፡ እግዚብሔር የፈጠረን፣ እኛ በእርሱ ስንረካ፣ በዚያ እርሱ እጅግ እንዲከብር ነው፡፡

ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ ለእግዚብሔር ክብር መኖር አለበት፡፡

እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት፡፡
1ቆሮንቶስ 1ዐ፡31

እግዚአብሔር ለክብሩ ከፈጠረን፣ ለእርሱ ክብር መኖር የሚኖርብን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ኃላፊነታችን የሚመጣው ከእቅዱ ነው፡፡ በመሆኑም፣ የመጀመሪያ ግዴታችን፣ እርሱ ለእኛ በሆነልን ሁሉ በመርካት የእርሱን ፋይዳ ማሳየት ነው፡፡ ይህ ነው እግዚአብሔርን የመውደድ (ማቴዎስ 22፡37) እና በእርሱ የመታመን (ዮሐንስ 5፡3- 4) መሠረታዊ ነገር፡፡ የእውነተኛ መታዘዛችን፣ በተለይም ሌሎችን የመውደዳችን (ቆላስያስ 1፡4-5) ሁሉ ሥረ ነገር ይህ ነው፡፡

ሁላችንም ማድረግ እንደሚገባን እግዚብሔርን አላከበርነውም፡፡

ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዙብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡
ሮሜ 3፡23

‹‹የእግዚብሔር ክብር ጎድሎአቸዋል›› ማለት ምን ማለት ነው? ማንኛችንም እንደሚገባን በእርሱ አልታመንም፣ አላከበርነውም ማለተ ነው፡፡ በታላቅነቱ ረክተን በእርሱ መንገድ አልሄድንም፡፡ እርካታን ከሌሎች ነገሮች በመፈለግ ከእግዚአብሔር የበለጡ ፋይዳዎችን አደረግናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ በመሠረቱ ጣኦት አምልኮ ነው (ሮሜ 1፡21-23) ኃጢአት ወደዓለም ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔርን እንደከበረ እርካታችን አርገን መቀበልን በጣም እምቢ በማለት ላይ ነን (ኤፌሶን 2፡3) ይህ በእግዚአብሔር ታላቅነት ላይ የሚደረግ አሰቃቂ በደል ነው (ኤርምያስ 2፡12-13)

ሁላችንም ከእግዚብሔር ተገቢ ፍርድ በታች ነን፡፡

የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና
ሮሜ 6፡23

ሁላችንም የእግዚብሔርን ክብር አንኳሰናል፡፡ እንዴት? ከእርሱ በላይ ሌሎች ነገሮችን በመምረጥ፡፡ ባለማመስገን፣ በእርሱ ባለመታመንና ባለመታዘዝ፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር ለዘላለም በክብሩ ደስተኞች እንዳንሆን በመከልከሉ ትክክል ነው፤ ‹‹እነርሱም ከጌታ ፊትና ከኃይሉ ክብር ተወግደው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ›› (2ተሰሎንቄ 1፡9

‹‹ገሀነም ወይም ስኦል›› የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ አሥራ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ አሥራ አንድ ጊዜ በኢየሱስ በራሱ፡፡ ይህ በተከፉ ወይም በተቆጡ ሰባኪዎች የተፈጠረ አፈታሪክ አይደለም፡፡ ኃጢአተኞችን ከፍርዱ ነፃ ለማውጣት ከሞተው የእግዚብሔር ልጅ የተላለፈ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ችላ ብንለው ከባድ አደጋ ነው የሚጠብቀን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰብዓዊ ፍጡር ሁኔታ የሚያደርገውን ትንታኔ እዚህ ላይ ቢያቆም ኑሮ፣ ተስፋ በሌለው የወደፊት ጭለማ ውስጥ እንወድቅ ነበር፡፡ ደግነቱ፣ ነገሩ እዚህ ላይ አይደለም የሚቆመው፡፡

እግዚአበሔር ሕይወትና ደስታን እንዲሰጠን አንድያ ልጁን ኢየሱስን ላከው፡፡

ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደዓለም መጣ...
1ጢሞቴዎስ 1፡15

ክርስቶስ እንደእኛ ላሉ ኃጢአተኞች መሞቱ ነው የምሥራቹ ፡፡ የሞቱን የማዳን ኃይል ዋጋ ያለው ለማድረግና የዘላለምን ሕይወት፣ እንዲሁም የደስታን በር ለመክፈት በአካል ከሞት ተነሣ፡፡ (1ቆሮንቶስ 15፡2ዐ) የዚህ ትርጉሙ፣ እግዚብሔር በደለኛ ኃጢአተኞችን ነፃ በማድረግም ፃድቅ ይሆናል ማለት ነው (ሮሜ 3፡25-26) ‹‹እንዲህም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለኃጢአት ሞቶአልና፤ ወደእግዚብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ፣ ስለአመፀኞች ሞተ›› (1ጴጥሮስ 3፡18) ወደ እግዚአብሔር መግባት ጥልቅና ዘላለማዊ እርካታ ባለበት ሥፍራ መሆን ነው፡፡

በክርስቶስ ደም ዓማካይነት የተገኙ ጥቅሞች፣ ንስሐ የሚገቡና በእርሱ የሚታመኑ ሰዎች የሚያገኙዋቸው ናቸው፡፡

በጌታ በኢየሱስ እመን፣ አንተም ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ ፡፡
ሐዋርያት ሥራ 16፡31

‹‹ንስሐ መግባት›› ማለት ፣ ውሸት ከሆኑት የኃጢአት ተስፋዎች ሁሉ መላቀቀ ማለት ነው፡፡ ‹‹እምነት›› ማለት፣ በኢየሱስ በኩል እንዲሆንልን እግዚአብሔር በሰጠን ተስፋዎች ሁሉ መርካት ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ ‹‹ ወደእኔ የሚመጣ ...ፈፅሞ አይጠማም ›› (ዮሐንስ 6፡35) ድነታችንን እራሳችን አናገኘውም፡፡ በችሎታችን ልናመጣው አንችልም (ሮሜ 4፡4-5) በእምነት ዓማካይነት በጸጋ ስጦታ ነው (ሮሜ 3፡24) ከነገሮች ሁሉ በላይ ዋጋ ከሰጠነው እናገኘዋለን (ማቴዎስ 13፡44) ይህን ስናደርግ እግዚአብሔር በፍጥረት ላይ ያለው ዓላማ ይፈፀማል—እርሱ በእኛ ይከብራል እኛ በርሱ እንረካለን—ለዘላለም፡፡