ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/እ ግ ዚአ ብሔር ን ባ ልወደ ውስ ?

ከGospel Translations Amharic

ዘልለው ለመሐድ፦የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

Related resources
More By John Piper
Author Index
More About The Gospel
Topic Index
About this resource
English: For Your Joy/What If I Don’t Love God?

© Desiring God

Share this
Our Mission
This resource is published by Gospel Translations, an online ministry that exists to make gospel-centered books and articles available for free in every nation and language.

Learn more (English).
How You Can Help
If you speak English well, you can volunteer with us as a translator.

Learn more (English).

By John Piper About The Gospel
Chapter 4 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው

Translation by Desiring God


በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም፡፡
ዮሐንስ 3፡36
እነዚህም ወደዘላላም ፍርድ ፣ ጻድቃን ግን ወደዘላላም ሕይወት ይሄዳሉ፡፡
ማቴዎስ 25፡46
እነርሱም ከጌታ ፊትና ከኃይሉ ክብር ተወግደው በዘላላም ጥፋት ይቀጣሉ፡፡
2ተሰሎንቄ 1፡9

ደስተኞች በምንሆንባቸው ጊዜያት ለመሞት አንፈልግም፡፡ መከራችን የከበደ ሲመስለን ብቻ ነው የመሞት ምኞታችን ከፍ የሚለው፡፡ በነዚያ ጊዜያት በእርግጥ የምንፈልገው፣ ሞትን ሳይሆን ፋታ ነው፡፡ መልካሙ ጊዜ እንደገና ቢመጣ እንወዳለን፡፡ ስቃዩ እንዲሄድልን እንፈልጋለን፡፡ የምንወደው ሰው ከመቃብር ተነስቶ ቢመጣልን እንፈልጋለን፡፡ ሕይወትና ደስታን እንሻለን፡፡

ሞትን የጥሩ ሰው ሕይወት ፍፃሜ አድርገን ስናቀርብ እራሣችንን ነው የምናታልል፡፡ ሞት ጠላት ነው፡፡ ከዚህ ዓለም አስደናቂ ደስታዎች ሁሉ ይለየናል፡፡ ሞትን በጥሩ ስም የምንጠራው ከክፉ ነገሮች ሁሉ አናሳ እንደሆነ አድርገን ነው፡፡ በስቃያችሁ ላይ የሚፈፀመው የሞት ፍርድ የመከራችሁ ሳይሆን፣ የተስፋችሁ ፍፃሜ ነው፡፡ የሰዎች ልብ ናፍቆት፣ መኖርና ደስተኛ መሆን ነው፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረን፣ ‹‹በሰዎች ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ›› (መክብብ 3፡11) በሚለው ሁኔታ ነው፡፡ የተፈጠርነው በእግዚአብሔር አምሳል ነው፤ እርሱ ሕይወትን ስለሚወድ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ለዘላለም እንድንኖር ነው የተፈጠርነው፡፡ እንኖራለን፡፡ የዘላለም ሕይወት ተቃራኒ አለመኖር ነው፤ ሲኦል፡፡ ኢየሱስ ስለሞት ከማንም ይልቅ በመናገር፣ እርሱ የሚሰጠውን የዘላለም ሕይወት አለመቀበል ውጤቶቹ መጥፋት ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር አስከፊ ቁጣ መሆኑን በግልፅ ተናግሯል፡፡ ‹‹በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን፣ የእግዚአብሔር ቁጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም›› (ዮሐንስ 3፡36)፡፡

ይህ ለዘላለም የሚኖር ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ ‹‹እነዚህም ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ›› (ማቴዎስ 25፡46)፡፡ ይህ የሚያመለክተው፣ እግዚአብሔርን ችላ ማለት ወይም መናቅ ሊነገር የማይቻል ፍፁም ክፉ ነገር የመሆኑን እውነት ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ ‹‹ዓይንህ ብታሰናክልህ ጐልጉለህ አውጣት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዓይን ኖሮህ ወደእግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻላል፤ በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ ይጠፋምና›› (ማርቆስ 9፡47-48)