ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/እ ግ ዚአ ብሔር እ ን ዴት ሊወደ ኝ ይችላ ል?

ከGospel Translations Amharic

ዘልለው ለመሐድ፦የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

Related resources
More By John Piper
Author Index
More About The Gospel
Topic Index
About this resource
English: For Your Joy/How Can God Love Me?

© Desiring God

Share this
Our Mission
This resource is published by Gospel Translations, an online ministry that exists to make gospel-centered books and articles available for free in every nation and language.

Learn more (English).
How You Can Help
If you speak English well, you can volunteer with us as a translator.

Learn more (English).

By John Piper About The Gospel
Chapter 3 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው

Translation by Desiring God


በእርሱ እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን በደሙ በተደረገ ቤዛነት የኃጢአትን ይቅርታ አገኘን፡፡
ኤፌሶን 1፡7
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፡፡
ዮሐንስ 3፡16
ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርሰቶስ ስለእኛ ሞተ፣ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል፡፡
ሮሜ 5፡7-8

እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ልክ፣ በሁለት ነገሮች ታይቷል፡፡ አንደኛው ፡- ከሠራነው ኃጢአት ቅጣት እኛን በማዳን ሥራው የከፈለው መሥዋዕት መጠን ነው፡፡ ሌላው፣ በሚያድነን ጊዜ የነበረን ለድነቱ ተገቢ ያለመሆናችን መጠን ነው፡፡

የመስዋዕቱን ልክ ወይም ጠመን፣‹‹አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ›› (ዮሐንስ 3፡16) በሚሉት ቃላት ውስጥ ልንሰማ እንችላለን፡፡ ‹‹ክርስቶስ›› በሚለው ቃል ውስጥም እንሰማዋለን፡፡ ይህ ክርስቶስ፣ ወይም ‹‹የተቀባ›› ወይም ‹‹መሲህ›› በሚለው ግሪክኛ ቃል ላይ የተመሠረተ ስም ነው፤ የታላቅ ክብር መገለጫ ቃል ፡፡ መሲሁ የእስራኤል ንጉሥ የሚሆን ነበር፡፡ ሮማውያንን ድል አድርጎ ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታን ያመጣ ነበር፡፡ ሲጠቃለል እንግዲህ፣ ኃጢአተኞችን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር የላከው ሰው፣ የእርሱ ልጅ ነበር፤ አንድያ ልጁና የተቀባ የእሥራኤል ንጉሥ፣ እርግጠኛው የዓለም ንጉሥ (ኢሳይያስ 9፡6-7)፡፡

ክርስቶስ ያለፈበትን አሰቃቂ ሞት በዚህ ግንዛቤ ላይ ስንጨምርበት፣ በአብና በወልድ የተከፈለው መስዋዕት፣ ለመግለጥ በማይቻል ሁኔታ ታላቅ፣ በመለኮትና በሰው መካከል ያለውን እርቀት ስንመለከት ደግሞ ፍፁም ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ይህን መስዋእት መረጠ፡፡

ይህ የማይገባን መሆናችንን በተረዳን መጠን፣ ለኛ ያለው ፍቅር መጠን ይጨምራል፡፡ ‹‹ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርሰቶስ ስለእኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ያሳያል›› (ሮሜ 5፡7-8) ፡፡ የሚገባን መለኮታዊ መስዋእት ሳይሆን፣ መለኮታዊ ቅጣት ነበር፡፡ እንዲህ ሲባል ሰምቻለሁ፡- ‹‹እግዚአብሔር ለእንቁራርቶች አልሞተም፤ እንደሰብዓውያን ለእኛ ፋይዳ ነበር አፀፋ የሚሰጠው ››፡፡ ይህ አባባል ፀጋን በራሱ ነው የሚያቆመው፡፡ እኛ ከእንቁራርቶች እጅግ የላቅን ነን፡፡ እንቁራርቶች ኃጢአት አልሠሩም፡፡ አላመኑም፤ እግዚአብሔርንም አስቆጥተው በሕይወታችን ላይ ፋይዳ ያለውን ነገር እንዳያከናውን አላደረጉም፡፡ እግዚአብሔር ለእንቁራርቶች መሞት አልተገባውም፡፡ አስከፊዎች አልነበሩም፡፡ እኛ ግን ነን፡፡ የነበረብን እዳ መለኮታዊ መስዋዕት ብቻ ሊከፍለው የሚችልና ታላቅ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለእኛ የፈፀመውን መስዋዕት የሚገልጥ አንድ ማስገንዘቢያ ብቻ ነው ያለው፡፡ እኛ አይደለንም፡፡ ‹‹እንደእግዚአብሔር ባለጠግነት መጠን›› (ኤፌሶን 1፡7) ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፡፡ የተገባን ነገር ስለሆነ የተሰጠ አፀፋ አይደለም፡፡ ፍፁም የሆነው የ ሙሉነት ነው፡፡ የመለኮታዊው ፍቅር መጨረሻም ይህ ነው፤ ለኃጢአተኞች ግንዛቤ የሚመስጥ ፍቅር፣ ታላቅ ዋጋ የተከፈለበት፡፡ ፍፁም የሆነ ውበቱ ከሁሉ በላቀ ሁኔታ ለዘላለም ደስተኞች የሚያደርገን ፡፡