ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/ለ ምን ድነ ው ሁሉ ነ ገ ር ከ እ ግ ዚአ ብሔር የ ተነ ሣ የ ሚሆነ ው?
ከGospel Translations Amharic
By John Piper
About The Gospel
Chapter 6 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው
Translation by Desiring God
- እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለኃጢአት ሞቶአልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ
1ጴጥሮስ 3፡18
- አሁን ግን እናንተ ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በከርስቶስ ደም አማካይነት ቀርባችኋል፡፡
ኤፌሶን 2፡13
- እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤ ፍፁም ደስታዬ ወደሆነው አምላክ እሄዳለሁ፡፡
መዝሙር 43፡4
ሁሉም ነገር ሲነገርና ሲከናወን፣ ወንጌሉ ወይም መልእክቱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ወንጌል ማለት ‹‹የምስራች›› ነው፡፡ ክርስትና መጀመሪያ ነገረ መለኮት ሳይሆን ዜና ነው፡፡ የጦር ምርኮኞች በተደበቀ ራዲዮ ዓማካይነት የሚያዳምጡት፣ አጋር ጦር በአቅራቢያው መድረሱንና ነፃ የመውጣታቸው ነገር የጊዜ ጉዳይ ብቻ መሆኑን የሚረዱበት ነው፡፡ ጠባቂዎቹ የምርኮኞችን ደስታ አይተው በምክንያቱ ግራ በመጋባት ይገረማሉ፡፡
በምሥራቹ ውስጥ ያለው የመጨረሻ ጥሩ ነገር ምንድነው? በአንድ ነገር ይፈፀማል፣ በእግዚብሔር በራሱ፡፡ የወንጌሉ ቃላት ሁሉ ወደሱ ይመራሉ፤ ይህ ካልሆነ የምሥራች አይደሉም፡፡ ለምሳሌ፣ ድነት ከሲኦል የሚያድን ብቻና ወደ እግዚአብሔር የማያደርስ ከሆነ፣ የምሥራች አይደለም፡፡ ‹‹ይቅርታ›› ከጥፋተኛነት የሚያሳርፍ ብቻ ከሆነና ወደ እግዚአብሔር መሄጃውን መንገድ የማይከፍት ከሆነ፣ የምሥራች አይደለም፡፡ ‹‹ጽድቅ›› በእግዚአብሔር ተቀባይነትን ብቻ እንጂ፣ ከእርሱ ጋር አንድነትን የማያመጣ ከሆነ ፣ የምሥራች አይደለም፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ መሆን›› ወደ እርሱ ቤተሰብነት ብቻ እንጂ በእጆቹ ላይ የማያሳርፈን ከሆነ፣ የምሥራች አይደለም፡፡
ይህ ወሳኝ ነገር ነው ፡፡ ብዙ ሰዎች ያለ እግዚአብሔር የምሥራቹን ብቻ ያቀፉ ይመስላሉ፡፡ ከሲኦል ለማምለጥ በመፈለጋችን ብቻ አዲስ ልብ ያለን ለመሆኑ እርግጠኛ ማስረጃ አይሆንም፡፡ ይህ ፍፁም የሆነ ተፈጥሯዊ ፍላጎት እንጂ፣ ልዕለ ተፈጥሮአዊ አይደለም፡፡ የይቅርታን ሥነ ልቦናዊ ፈውስ ለመፈለግ ፣ ወይም የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማስወገድ፣ ያለዚያም የእግዚብሔርን ዓለም ለመውረስ አዲስ ግንዛቤ አይፈልግም፡፡ እነዚህ ሁሉ ያምንም መንፈሳዊ ለውጥ የሚታወቁ ናቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች ለመሻት ዳግም መወለድ አያሻችሁም፡፡ አጋንንትም ይፈልጓቸዋል፡፡
እነዚህን መፈለግ ስህተተ አይደለም፡፡ አለመፈለጉ ሞኝነት ነው፡፡ የመለወጣችን ማስረጃ፣ እነዚህ ነገሮች ወደ እግዚአብሔር ደስታ የሚያደርሱን ስለሆኑ የምንፈልጋቸው መሆናችን ነው፡፡ ይህ ነው ክርስቶስ የሞተለትን ከሁሉ የላቀ ነገር፡፡ ‹‹እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለኃጢአት ሞቶአልና፤ ወደእግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቀ የሆነው እርሱ ስለዐመፀኞች ሞተ›› (1ጴጥሮስ 3፡18)፡፡
ለምንድነው ይህ የምሥራቹ ፍሬ ነገር የሆነው? ምክንያቱ፣ የእግዚአብሔርን ክብር በማየትና በመደሰት ሙሉና ዘላለማዊ ደስታን እንድንለማመድ መደረጋችን ነው፡፡ ከሁሉ የላቀው ደስታችን ከዚህ ካነሰ ነገር የሚመጣ ከሆነ ፣ ጣኦት አምላኪዎች ነን፣ እግዚአብሔርንም አላከበርነውም፡፡ የፈጠረን የእርሱ ክብር በዚያ ባለን ደስታ እንዲገለጥ አድርጎ ነው፡፡ የክርስቶስ ወንጌል በልጁ ሕይወት ዋጋነት የገኘ የምሥራች ነው፡፡ እግዚአብሔር አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያደረገው፣ ለዘላለምና ለሁልጊዜ በሚጨምር ደስታ ፣ ማለት በራሱ ሊመስጠን ነው፡፡
ክርስቶስ ከመምጣቱ ረዘም ባለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሙሉና ዘላለማዊ ደስታ ምንጭ አድርጎ እራሱን ገለጠ፡፡ ‹‹የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ ›› (መዝ. 16፡11) ፡፡ ከዚያ በኋላ ይሰቃይና ‹‹ወደእግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ›› ክርስቶስን ላከው፡፡ ማለት ክርስቶስን የላከው፣ ሰብዓዊ ፍጡር ሊኖረው ወደሚችለው እጅግ ጥልቅና ረጅም ደስታ እንዲያደርሰን ነው፡፡ ጥሪው ወይም ግብዣው እንዲህ ይላል፣ ‹‹በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ›› (ዕብራዉያን 11፡25) ተመለሱና ‹‹ወደዘላለም ደስታ ኑ››፡፡ ወደ ክርስቶስ ኑ፡፡