ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/ኢየ ሱስ ለ ምን ድነ ው መሞት የ ነ በ ረ በ ት?
ከGospel Translations Amharic
By John Piper
About The Gospel
Chapter 2 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው
Translation by Desiring God
- ‹‹በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተስረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኃጢአት ሳይቀጣ በትእግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው ››
ሮሜ 3፡25
- "‹‹ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ እንደወደደንና ስለኃጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው›› 1ዮሐንስ 4፡1ዐ ‹‹ክርሰቶስ ስለ እኛ ርግማን ሆኖ ከሕግ ርግማን ዋጅቶናል››
ገላቲያ 3፡13
እግዚአብሔር ፍትሐዊ (ጻድቅ) ባይሆን ኖሮ የገዛ ልጁን ለሥቃይና ለሞት አሳልፎ አይሰጥም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ባይሆን ኖሮ አንድያ ልጁን በፈቃደኝነት አሳልፎ አይሰጥም ነበር፡፡ እርሱ ፍትሐዊ (ጻድቅ)፣ አፍቃሪ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ፍቅሩ የርሱን ፍትሐዊ ነት ለማሟላት ፈቃደኛ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ሕግ፡- ‹‹አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ›› ይላል፤፡፡ ዘዳግም 6፡5፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ሌሎች ነገሮችን ከእርሱ አስበልጠን ወድደናል፡፡ ኃጢአት ማለት ይህ ነው ፤ ሌሎች ነገሮችን ከእግዚአብሔር አስበልጠን በመምረጥ እርሱን ሳናከብረው ስንቀርና የመረጥናቸውን ነገሮች ስናደርግ፡፡ ሮሜ 3፡23፣ ‹‹ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል›› ይላል፡፡ የምናከብረው በጣም የሚያስደስተንን ነገር ብቻ ነው፤ ያም እግዚአብሔር አይደለም፡፡
ስለዚህ ኃጢአት በጣም ትልቅና በክቡር እግዚአብሔር ላይ የሚፈጸም በደል ስለሆነ ነው ትንሽ አይደለም፡፡ የስድብ ከባድነት የሚያርፈው፣ በተሰዳቢው ክብር ላይ ነው፡፡ የዓለማችን ፈጣሪ እግዚአብሔር የእኛ ፍፁም አክብሮት፣ አድናቆትና ታማኝነት ይገባዋል፡፡ ስለዚህ እርሱን አለመውደድ ስሕተት ሳይሆን፣ ክህደት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር ዝቅ ያደርጋል፣ የሰውን ደስታም ያጠፋል፡፡
እግዚአብሔር ፍትሐዊ እንደ መሆኑ መጠን የምንሠራቸውን ኃጢአቶች ዝም ብሎ ማየት አይሆንለትም፡፡ ቅዱስ ቁጣ ስለሚቆጣ ቅጣት ይገባቸዋል፡፡ ይህንንም ሮሜ 6፡23 ውስጥ ግልጽ አድርጓል ‹‹የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና፡፡›› ሕዝቅኤል18፡4 ውስጥ ደግሞ፣ ‹‹ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች›› ይላል፡፡ በኃጢአት ላይ የሚያንጃብብ ቅዱስ እርግማን አለ፡፡ ኃጢአትን አለመቅጣት፣ ፍትሃዊ አለመሆን ነው፡፡ እግዚአብሔርን አለማክበርም ትክክል ሁኖ ሊታይ ነው፡፡ ውሸት በእውነት ላይ ይነግሣል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‹‹በሕግ መጻሕፍት የተጻፈውን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው›› (ገላትያ 3፡1ዐ፤ ዘዳ. 27፡26) የእግዚአብሔር ፍቅር ግን በኃጢአተኛ ሰብዓዊ ፍጡራን ሁሉ ላይ ከሚያንጃብበው እርግማን ጋር አይሆንም፡፡ በመሆኑም ቁጣውን ይሸከምና በርሱ የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ እርግማን ይሸከም ዘንድ እግዚአብሔር የራሱን ልጅ ላከ፤ ‹‹ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል›› (ገላትያ 3፡13)፡፡
ሥርየት የሚለው ቃል ትርጉም ይህ ነው፡፡ የሚገልጠው ምትክ በማቅረብ የእግዚአብሔርን ቁጣ ስለማስወገድ ነው፡፡ ምትክ የተሰጠው በእግዚአብሔር በራሱ ነው፡፡ ምትክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን፣ ወደራሱ አዛወረው፡፡ ነገር ግን በረደ እንጂ አልተሠረዘም፡፡ በእግዚአብሔር አንቀልድ ወይም ፍቅሩን አናቃል፡፡ የኃጢአታችንን ከባድነትና በእኛ ላይ ያለውን ቁጣ ተገቢነት ካልተገነዘብን፤ በእግዚአብሔር በመወደዳችን እየተደነቅን ፊቱ ለመቆም አንችልም፡፡ ለዚህ ዕድል የማንበቃ መሆናችንን በፀጋ ዓማካይነት ስንረዳ ግን፣ ወደ ክርስቶስ ስቃይና ሞት ተመልክተን እንዲህ እንላለን፡- ‹‹ፍቅር ይህ ነው፣ እኛ እግዚአብሔርን እንደወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ እንደወደደንና ስለኃጢአታችን ማስተሰረያም ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው›› (1ዮሐ. 4፡1ዐ)