ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/መግ ቢያ

ከGospel Translations Amharic

(በ2ቱ እትሞቹ ዘንድ ያለው ልዩነት)
ዘልለው ለመሐድ፦የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
(ገጹን «For Your Joy/Introduction» ቆለፈው። ([edit=sysop] (ያልተወሰነ) [move=sysop] (ያልተወሰነ)))
(«For Your Joy/Introduction» ወደ «ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው/መግ ቢያ» አዛወረ)

እትም በ19:42, 19 ኤይፕርል 2018

Related resources
More By John Piper
Author Index
More About The Gospel
Topic Index
About this resource
English: For Your Joy/Introduction

© Desiring God

Share this
Our Mission
This resource is published by Gospel Translations, an online ministry that exists to make gospel-centered books and articles available for free in every nation and language.

Learn more (English).
How You Can Help
If you speak English well, you can volunteer with us as a translator.

Learn more (English).

By John Piper About The Gospel
Chapter 1 of the book ስለ ኢየሱስየሚጠየቁ ጥያቄዎችናመልሶቻቸው

Translation by Desiring God


ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ደቀመዛሙርቱ በጊዜው በህዝቡ ዘንድ ይወራ ስለነበረው ነገር አንስተው ሲነጋገሩ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፡- ‹‹ለመሆኑ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?››፡፡ ስለእርሱ ማንነት የተባለውን ነገር ሁሉ ዘርዝረው ነገሩት፡፡ ሰዎች ስለሚሉት መጠየቁን ትቶ ትኩር ብሎ እያያቸው፣‹‹እናንተስ ማን ትሉታላችሁ?››፡፡

ሌሎች ሰዎች ስለእርሱ የሚያወሩትን መግለጥ ለደቀመዛሙርቱ በጣም ቀላል ነበር፡፡ እኛም ብንሆን ከኢየሱስ ጥያቄ ጋር የምንፋጠጥበት ጊዜ ይኖራል፡፡ ማነው እንላለን?

በተደጋጋሚ የምንሰማው በጣም የተለመደ መልስ አለ፡፡ ይህም ኢየሱስ ታላቅ የግብረ ገብ መመህር ፣ የሚል ነው፡፡ ለአብነት የሚበቃ ፣ እንዲሁም ጠቢብና ርህሩህ ነበረ›› የሚል ነው፡፡

‹‹አንበሳው ጠንቋይዋና ቁምሳጥን›› የተሰኘ መጽሐፍ የደረሰ ሲ ኤስ ሊዊስ የተባለ እንግሊዛዊ ጸሐፊ እንዲህ በማለት እህን የማሳነስ አስተሳሰብ ማስወገድ እንዳለብን ይናገራል፡፡

እዚህ ላይ ለመከላከል በመሞከር ላይ ያለሁት፣ ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለኢየሱስ

የሚሉትን ሞኝነት የተሞላበት ነገር የሚናገርን ሰው ነው፡፡ ይህም የሞኝነት ነገር ‹‹ኢየሱስን እግዚአብሔር ነኝ በሚለው አገላለፁ ሳይሆን፣ እንደታላቅ የሞራል መምህር ልቀበለው ዝንጁ ነኝ›› ይላል፡፡ ልንለው የማይገባ አንድ ነገር ይህ ነው፡፡ በሥጋ ያለ ሰው ኢየሱስ ያስተማራቸውን ትምህርቶች ቢያስተምር እና የተናገረውን ቢናገር፣ ታላቅ የግብረገብ አስተማሪ ነው አይባልም ነበር፡፡ እንዲህ ያለ ሰው እብድ (እኔ የተቀቀለ እንቁላል ነኝ ብሎ እንደሚያምን ሰው ያለ እብድ) ወይም ደግሞ ከገሃነም የመጣ ሰይጣን ነው ይባል ነበር፡፡ የራሳችሁን ምርጫ ልታደርጉ ይገባል፡፡ ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፣ ነውም፤ ያለዚያ እብድ ወይም ሰይጣን ነው፡፡ ዝም በል አንተ ሞኝ ልትሉት፣ ልትተፉበት ወይም እንደ ሰይጣን ልትገስጹት ትችላላችሁ፣ ወይም እግሩ ሥር ወድቃችሁ ጌታ እና እግዚአብሔር ብላችሁ ልትጠሩት ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ታላቅ የግብረገብ አስተማሪ ነው የምንለውን ትርጉም የለሽ ነገር መተው ዓይነት ምርጫም አልተወልንም፡፡

ይህ ኢየሱስን ማን ነው የምትሉት? የሚለው ጥያቄ ልትጠይቁትና እንዲሁም ልትመልሱት የሚገባ በጣም አስፈላጊ ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ጆን ፓይፐር የተባለ ጸሐፊ ስለ ኢየሱስ የሚጠየቁትን በጣም የተለመዱ ጥያቄዎች ማለት፤ ማን ነው ? ለምን መጣ? የሠራው ሥራ ምንድነው? እና ስለዙህ ጉዳይ ለምን ግድ ሊለን ይገባል? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክራሉ፡፡

ከነዚህ ጥያቄዎች አንዳንዶቹን ጥይቃችሁ ከሆነና፣ በራሳችሁ አሳብና ንድፈ አሳብ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረቱ አንዳንድ መልሶች በመፈለግ ላይ ከሆናችሁ፣ ከእኛ ጋር እንድትገናኙ እንጋብዛችኋለን፤ ለራሳችሁ ደስታ፡፡